"Tanadar" Текст песни
"Tanadar" имеет текст на языке Тигринья.
Значение «Tanadar» исходит из языка Тигринья и в настоящее время не преобразуется в перевод на английский язык.
Wendi Mak / ወንዲ ማክ - ጣና ዳር / ማለዳ - Tanadar / Maleda Ethiopian Music 2023(Official Video)
Any unauthorized use, copying or distribution is strictly prohibited By Wendi Mak.
Copyright ©2023: Wendi Mak .
#Tanadarmaleda #wendimak #ethiopianmusic #ጣናዳር #ማለዳ
__________________________________________
ጠይም ማሳ መሳይ የውብ ዳር(×2) ውቢቷ
ጎንደር ደምቢያ መስኩ ጣና ዳር ነው ቤቷ(×2)
????????????????
የሀር ቀሚስ ጥልፏ አልቦና ድጎቷ
ድምቀትን ሰጥቷታል ለመላው ውበቷ
ፀሃይ መከለያ ዣንጥላዋ ያምራል
ያገር ቤቷ ጎበል አይኗ ያባብላል
ያገር ቤቷ ጎበል አይኗ ያባብላል(×4)
????????????????
ወተት የመሰሉ ጥርሶቿ ያምራሉ
አይኖቿ ተኮልተው በሩቅ ያሳሳሉ
በወገቧ ወርዶ ድሪማርዳው ጌጡ
እሷን ያየ ሁሉ ጠፋው መላቅጡ
እሷን ያየ ሁሉ ጠፋው መላቅጡ(×4)
????????????????
ንገረኝ ይሉኛል ምኗ እንደሚናፍቅ(×2)
አላያት ሰው ሁሉ ስትጫወት ስትስቅ(×2)
አንደበቷ ማር ነው እሷ ምኑን አውቃ(×2)
ታይታም ታፈዛለች እንኳንስ ተናፍቃ(×2)
ማለዳ(×3) መጥተሽ ማለዳ መጥተሽ
አቦሉን ጠጥተሽ ትመለሻለሽ(×2)
ማለዳ(×3) መጥተሽ ማለዳ መጥተሽ
አቦሉን ጠጥተሽ ትመለሻለሽ(×2)
????????????????
መንገደኛ እንዳለ ወደዚያች ልጅ ሀገር(×2)
ናፍቆት ቢያደርስልኝ ምናለ ቢቸገር(×2)
ደህና ነው እያሏት መጥታም አትጠይቀኝ
ይልቁን ሂዱና ናፍቆሻል በሉልኝ(×2)
ማለዳ(×3) መጥተሽ ማለዳ መጥተሽ
አቦሉን ጠጥተሽ ትመለሻለሽ(×2)
ማለዳ(×3) መጥተሽ ማለዳ መጥተሽ
እኔን ሳታገኚኝ ትመለሻለሽ(×2)
አቦሉን ጠጥተሽ ትመለሻለሽ(×2)
????????????????
የአክሊሉ ስዩምና ጋሻው አዳል ማስታወሻ
__________________________________________